የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራልን በህግ ፊት እንታደግ ዘንድ የቀረበ የእርዳታ ጥሪ።

ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በስደተኛ ኢትዮጵያውያን በ1987 እ.ኤ.አ ተመሰረተች። ብዙ ፈተናዎችንም በማለፍ በልጆችዋ ትጋት እና በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተራዳዒነት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን የሚያኮራ ካቴድራል እስከመገንባትም ደረሰች። ዛሬ ግን በቤተክርስትያናችን ስር ተሰብስበን ለሀገራችን ሰላም መፀለይ በሚገባን ሰዓት ፤ ስለልጆቻችንን የወደፊት ህይወት እና ቤተክርስትያናዊ ልማት መትጋት በሚኖርብን ወቅት ካቴድራላችንን እና ማህበረ ምዕመናንን ያገለግሉ ዘንድ በተደጋጋሚ የመረጥናቸው የቦርድ አባላት ከኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር በራቀ ድርጊት እመቤታችንን እና አገልጋይ ልጆችዋን ማሳዘን ስራቸው ኣድርገዋል። ከሀያ ሁለት ዓመታት በላይ ያገለገሉንን ብፁዕ አባት አቡነ ያዕቆብን ህግን ባልተከተለ መንገድ ለማሰናበት ከመወሰን አልፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ቀኖናዋን እና ትውፊትዋን ለማዳን የተሰደደውን እና የሁላችንም ተስፋ የሆነውን ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ አንቀበልም እስከ ማለትም ደረሱ።

በሚያሳዝን ሁኔታ በሎንዶን እና በዋሺንግተን የታየውን ሴራ በአትላንታም ሊደግሙት ከጅለዋል። ስደተኛው ህዝባችን ሁለት ስራ ሰርቶ ለቤተክርስትያናችን የቆጠበውን ገንዘባችንን በብዙ ሺዎች ዶላሮች በማውጣትም ለእኩይ ተግባራቸው የህግ ጠበቃ ቀጥረዋል። ወገኖቻችን፤ ዛሬ ህዝባችን በአምባገናዊ የመንግስት ስርዓት እያተሰቃየ ይገኛል። እዚህ ነፃነት እና ሰላም የበዛበት የስደት ሀገራችን ላይ ሊሰፍን የሚሞከርን አምባገነናዊ ስርዓትን ግን በጋራ እውነትን ይዘን ልንታገለው ይገባል። ለዚህም የተዘጋጀውን የህግ አገልግሎት ፈንድ ለመርዳት የበኩላችንን እንወጣ ዘንድ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም እንማፀናለን።

የሚኖርዎትን ጥያቄ በአግባቡ እንመልስ ዘንድ የስልክ ቁጥርዎን ወይም የኢሜይል አድራሻዎትን ያካፍሉን እና ስለጉዳዩ ያለውን መረጃ ሁሉ (በተለይም የሚሰበሰበውን የእናንተው የገንዝብ እርዳታ አስመልክቶ) በየጊዜው እናደርስወታለን።

Help us defend Atlanta Sealite Mihiret Saint Mary Ethiopian Orthodox Church

Sealite Mihret Kidist Mariam Cathedral in Atlanta, established in 1987, has been serving the Ethiopian American community in Metro-Atlanta area for well almost three decades. Our church, despite passing through many trying and difficult times, had overcome its problems and even succeeded to build a beautiful cathedral with the hard work of all Ethiopians regardless of different backgrounds and even religion. Unfortunately, our cathedral today is facing a challenge that it has never seen since its inception.

At a time our people back in Ethiopia are suffering from historical challenges, certain elected board members of the Cathedral have illegally attempted to terminate our archbishop Abune Yaekob, who has been serving our church for over two decades. Moreover, these individuals repeatedly failed to implement our Holy Synod directives and undermined the very nature of our Holy Synod in exile. Dear brothers and sisters, we are saddened to see what happened in London, England and Washington D.C. is now repeating itself in Atlanta. On the top of that, they are wasting thousands of dollars by suing their fellow board members and Abune Yaekob in a civil court.

Brothers and sisters, in the name of our God the almighty, and Sealite Mihret Kidist Mariam, we ask your help to support the legal fund that we have established for this cause. If you give us your number, we will be glad send you up to date information about the status of the case, financial disclosure and other information. Because it is your case too. If you have any questions, please do not hesitate to contact us.

 

Concerned Members of Sealite Mihiret Kidist Mariam Church
Help spread the word!

492total visits,1visits today