አባቶች የሰሩትን የጥንት ድንበር አታፍርስ

«አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ» (ምሳ 22-28) ቅዱስ ሲኖዶስ ምንድነው? ቅዱስ ሲኖዶስ ጥንቷዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባዔ ነው ።የመጀመሪያው ሲኖዶስ በርዕሰ ሐዋርያት በፓትርያርክ ጴጥሮስ ይመራ ነበር። በዚህም ዘመን በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት/በፓትርያርክ የሚመራ ከሐዋርያት ጀምሮ የነበረ ጉባኤ ነው ።የቅዱስ ሲኖዶስ ዋናና ትልቁ ሥራው ለምእመናን መንፈሳዊ መመሪያ መስጠት ነው። ምእመናን ለመምራት ደግሞ […]

   መናፍቅነት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ

የመገንጠል አዝማሚያ ያላቸው የመናፍቃን ባሕርያት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን Sectarian Mind-Set within the Realm of Orthodoxy   በአለንበት ዘመን አንዱ ከምንም ተነስቶ ባልገባው ነገር በአንዱ ላይ “መናፍቅ” የሚል ቅጽል መለጠፍና ማሸማቀቅ የተለመደ ተገባር እየሆነ መጥቷል። በተቃራኒው ደግሞ ወንጌላዊነትን ለዝነኝነትና በዚሁም ሰበብ ለገንዘብ መሰብሰቢያ መጠቀሚያ በማድረግ በመዝሙርም ሆነ በትምህርት ከተለመደው ወጣ ባለ ሁኔታ በራሳቸው የልብ ወልድ መንገድ […]

ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የማያምን መንፈስ 

  በብፁዕ አቡነ በርናባስ ላይ የስድብ ዘመቻ ለጀመሩት ቢጽ ሐሳውያን ከሳሾች የተሰጠ መልስ (ክፍል ሁለት ) በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ መልአኩ « የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ » 1 ዮሐ 4፥ 1-3፤ የዘመናችን ቢጽ ሐሳውያን፥ በሌላቸው ሥልጣንና […]

እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል

ሙሉውን ለማንበብ ይሕን ይጫኑ

ውግዘት ምንድን ነው? What is excommunication?

በመምሕር ታሪኩ ኣበራ ለውግዘት የሚያበቁ ምክንያቶችስ ምን ምን ናቸው? What are the reasons of excommunication? «ኤጲስቆጶስ በማይገባ አያውግዝ ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባ ቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት።»ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5፥184 ውግዘት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን ትርጓሜውም መለየት ማለት ነው።ውግዝት የሚተላለፈውም አንድ የቤተክርስቲያን ተከታይ የሆነ አገልጋይም ሆነ ምዕመን ከእውነተኛው የመጽሐፍ […]

ፍትሕና እውነት ለኢትዮጵያ አንድነት

  መጋቢ አዲስ መምህር ልዑለ ቃል አካሉ ሲአትል በተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ ላይ ያቀረቡት ዝግጅት። ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

ወደ ተርሴስ ጉዞ ይቁም!

እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ባርኮ፣ ቀድሶ እና አክብሮ ከአራት የስጋና ከሶስት የነፍስ ባህሪያት የፈጠረው፤እንዲያመልከው፣ እንዲያመሰግነውና እየታዘዘ ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንዲኖር ነው።በተጨማሪም ወንድና ሴት አድርጎ ፈጥሮ፤ብዙም ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ በሰላምና በህብረት እንዲኖሩባትና ምድርን እያበጃጁ እንዲጠቀሙባት አዘዛቸው። ነባቢ፣ ልባዊና ህያው ሆኖ በእግዜብሔር አምሳል የተፈጠረው ሰው፤ የአምላክን ትዕዛዝ ጥሶ አትብላ የተባለዉን ሲበላ የመጀመሪያዉን የወደ ተርሴስ ጉዞ ጀመረ። ከእግዚአብሔር […]

ስለ አባላት ልዩ ጉባኤ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ

ለአትላንታ ቅድስት ማርያም ካቴድራል አባላት ስለ ፍርድ ቤት በተለይም ልዩ የኣባላት ስብሰባ ስለመጠራቱ የተለያዩ እውነትነት የሌላቸው መረጃዎች በተለያዩ የከተማችን ሚዲያዎች ሲናፈሱ ቆይተዋል እውነትን ለሚፈልጉ ሳይበረዝ ሳይከለስ ሕዝቡ እንዲያየውና እውነትና ሀሰቱን ተረድቶ የሕሊና ፍርዱን እንዲሰጥ ሙሉውን መረጃ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል አሉ።

በአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ካቴድራል በከሳሾቹ የቦርድ አባላት የሚፈጽሙት ተግባር ቅጥ አምባሩ የጠፋው ነው። እነ አቶ አባተ ቤተክርስቲያኗን በቀጥታ ለማህበረ ቅዱሳን የዳግም ትንሳኤ እለት ለማስረከብ ዝግጅታቸውን እያገባደዱ ነው። በሚጪው እሁድ  ጋብዘነዋል ያሉት «መምህር» የኦሀዮ ገብርኤል ከፋፍሎ ያፈረሰ እና የአስተዳደር ቦርዱ ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ በህገ ወጥ መንገድ ያዘዋወረ ነው።(ደብዳቤውን ይመልከቱ)። ያሬድ ኢትዮጵያ እያለ ሀመር የሚባለው […]